እሮጣለሁ
Erotalehu
2006 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማዳኑን አይቻለሁ ምስክሩ ሆኛለሁ
ሥራውን አወራለሁ ጌታዬን አከብራለሁ
ከጌታ የተነሳ ነው በህይወት የምኖረው
ከኢየሱስ የተነሳ ነው ዛሬም የምዘምረው
ቁጥር 1 · Verse 1
ምህረቱ ቸርነቱ ለአኔ በዝቶልኝ ነው
የትናንቱን እየረሳሁ የዛሬውን ልጨብጥ
ወደፊት እዘረጋለሁ በአዲስ መገለጥ
ካየሁት ወደሚበልጠው ክብር እሮጣለሁ
ካወቅሁት በላይ ለማወቅ እገሰግሳለሁ
እሮጣለሁ እስከመጨረሻ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ይህ ነውና የእኔ ድርሻ
እጋደላለሁኝ መልካም ገድል
ከእጁ ለመውሰድ የፅድቅ አክሊል
የእውነትን ቃል በቅንነት እየተናገርኩኝ
የምሥራቹን ለፍጥረት እያበሰርኩኝ
የማላሳፍር ሠራተኛ ሆኜ በዚች ምድር
እተጋለሁኝ እሩጫዬን ልፈጽም ዘወትር
መልካሙን ገድል ተጋድዬ ሩጫዬን ስጨርስ
ሐይማኖቴንም ጠብቄ ወደ ሀገሬ ስደርስ
ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያኔ ይሸልመኛል
የተዘጋጀልኝን አክሊል ያስረክበኛል
አዝማች · Chorus
መዳኔን አይቻለሁ ምስክሩ ሆኛለሁ
ሥራውን አወራለሁ ጌታዬን አከብራለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ