አንተ ነህ አባቴ
Ante Neh Abatie
2006 · ትራክ 8 · 6:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው እንዳለህ አይደለህም አእምሮ እንዳሰበህ
ከመጣው ሁሉ ታልፋለህ ከተነገረልህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ከሚሉህ በላይ ነህ ጌታ
ከሚሉህ በላይ
ከሚሉህ በላይ ነህ አምላኬ
ከሚሉህ በላይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙዎች አውቀናል እንዳሉ
በራሳቸው አእምሮ እንዳሰሉ
አንተ ግን እንደዛ አይደለህም
ትልቅ ነህ ማንም አያውቅህም
አስገረመኝና ሥራህ
ማልጄ ተነሳሁ ላመልክህ
ፈቃዴን ሰጠሁ እራሴን
ግዛኝ ኢየሱሴ
አዝማች · Chorus
ግዛኝ ኢየሱሴ (፰x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አላፋው አግዳሚው እንዳለህ
አውቀናል ብለው እንዳወሩ
ሺህ ቃል ቢደረደር አይገልፅህ
አምላኬ ከመባል ታልፋለህ
በትላንቱ ነገር ስገረም
ዛሬም አስደነቅከኝ ዳግም
ተዓምራትህ በዛ በሕይወቴ
አንተ ነህ አባቴ
አንተ ነህ አባቴ (፲x)
አዝማች · Chorus
እስከመቼ ያልኩኝ ፍቺ ላጣው ህልሜ
ምላሽን ሰጥቶኛል እንዳልቀር ደክሜ
ጌታ ባየኝ ወራት እንዲህ ሆኖልኛል
አንደበቴም ሁሉ ዛሬማ ምሥጋናን ያወራል
ዘመርኩበት ባለቀስኩበት
ዘመርኩበት አይሆንም ባልኩበት
ዘመርኩበት ባጉረመረምኩበት
ዘመርኩበት በጠላቶቼ ፊት (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ምንም ታናሽ ቢሆን ጅማሬው የተነሳበት
ፍፃሜው ትልቅ ነው በአምላኩ የሚደርስበት
እጅህን አታንሳ በድፍረት ጌታ በገባው ላይ
ስለ እርሱ ተዋጊ ተሟጋች አለና በሰማይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ