ሀዘኔን በአንተ ጥያለሁ
Hazenien Bante Teyalehu
2006 · ትራክ 5 · 3:56 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በምንም አልሰጋም ልቤም አይደነግጥ
በሆነው ባልሆነው ምንድን ነው መናወጥ
ስለ ነገ እያሰብኩ እኔ አልጨነቅም
እግዚአብሔር ሳያውቀው በእኔ የሚሆን የለም
አዝማች · Chorus
እኔማ
ሀሳቤን በአንተ ጥያለሁ
ሀዘኔን በአንተ ጥያለሁ
ሸክሜም ይኸው በፊትህ
ናፍቆቴ መኖር በእረፍትህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለማይሞልውና ለዚህ ዓለም ነገር
ታዲያ ለምንድን ነው መጨነቅ መሸበር
ትላንት ዛሬ አይደል ይህንን አውቃለሁ
ጠላት ይስማው እንጂ ድሌን ዘምራለሁ
አዝማች · Chorus
እኔማ
ሀሳቤን በአንተ ጥያለሁ
ሀዘኔን በአንተ ጥያለሁ
ሸክሜም ይኸው በፊትህ
ናፍቆቴ መኖር በእረፍትህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ምክኒያቱ ጌታ ነው ዛሬን ለመኖሬ
ስንቱን በእርሱ አልፌ ስንቱን ተሻግሬ
እግዚአብሔር ስላለኝ ነገንም ደፍራለሁ
ዘመኑን ዋጅቼ በቀኑ ኖራለሁ
አዝማች · Chorus
እኔማ
ሀሳቤን በአንተ ጥያለሁ
ሀዘኔን በአንተ ጥያለሁ
ሸክሜም ይኸው በፊትህ
ናፍቆቴ መኖር በእረፍትህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ነፍሴ አትማረሪ አታስጨንቂኝ
እግዚአብሔር ያለው ነው የሚሆንልኝ
በሰው አልታመን እኮ ሥጋ ለባሹን
ጌታ ይሰጠኛል መከናወኔን
እ ነፍሴ አትማረሪ
እ አታስጨንቂኝ
እ እግዚአብሔር ያለው ነው
ተዪኝ የሚሆንልኝ
እ በሰው አልታመንኩ
እ ሥጋ ለባሹን
እ ጌታ ይሰጠኛል
ተዪኝ መከናወኔን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ