የቤቴ እራስ ነህ
Yebietie Eras Neh
2006 · ትራክ 2 · 5:44 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መሰዊያዬን ልስራ ከማጠኔ በፊት
ከድንኳኔ ላውጣ አንተ የማትከብርበትን አዎ
እንጨቴን ልረብርብ አንድደው እሳቴን
መስዕዋት አድርጌ ላስቀምጠው እራሴን (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተን ደስ ካለህ አምልኮዬ
አንተን ካከበረህ ኑሮዬ
ክበርልኝ ጌታዬ (፪x)
ክበርበት ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የመኖሬ ሚስጥር የመክበሬ ጅምር
አንተ አይደለህም ዎይ እግዚአብሔር (፬x)
የእኔ ከፍታዬ
አንተ አይደለህም ዎይ ጌታዬ (፪x)
የእኔ የብቻዬ
አንተ አይደለህም ዎይ ጌታዬ (፪x)
መከበሪያዬ
አንተ አይደለህም ዎይ ጌታዬ (፪x)
የእኔ ማረፊያዬ
አንተ አይደለህም ዎይ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰማይን በስንዝር የለካህ
ምድርንም በቃልህ ያፀናህ
እግዚአብሔር አንተ ትልቅ ነህ (፬x)
አዝማች · Chorus
አላክብር አላምልክ
የልቤ ጌታ ነህ
አላርክ አላነግሥ
የቤቴ እራስ ነህ
ላይ በሰማይ በዙፋንህ ሆነህ
በምድር ያለውን ሁሉን ትገዛለህ
የሚሳንህ የለም ሁሉን ትችላለህ
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ