ከፍታዬን ልያዝ
Kefetayien Leyaz
2006 · ትራክ 6 · 5:05 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የጠላቶች ቁጣ ቢነድም በላዪ
ከእነርሱ ይበልጣል አዎ የጠራኝ ጌታዬ
ልቤም አይደነግጥ በወጀቡ ብዛት
መንገድ ላይ አይጥለኝም ጌታ እኔ የታመንኩበት (፪x)
ወጀቡን አይቼ ፀጋዬን አልጥልም
የከበረውን ነገር አዎ ለውሾች አልሰጥም
እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ጉልበቴ አይላላም
በጠላቴ ዛቻ እኔ ስፍራዬን አልለቅም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከፍታዬን ልያዝ ተራራውን
እግዚአብሔር ለእኔ ያየልኝን
አልደከምኩም ዛሬም ጉልበታም ነኝ
የሰማሁት ወንጌል አላረጀም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዮርዳኖስን አይተው እህ ሰዎች ብዙ ቢሉ
እኔ እሻገራለሁ ሰምቻለሁ ቃሉን አዬ
ሰምቻለሁ ቃሉን
ካየልኝ በረከት እህ ከግቤ ላይ ሳልደርስ ኦሆ
ወጀቡን አይቼ እኔስ አልመለስም አዬ
እኔስ አልመለስም
እልፍ በል ያለኝ ጌታ ከእኔ ጋር ነው
መንገዴን ጀምሬ እንዴት እመለሳለሁ
ከእኔ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል
ልቤም ላይደነግጥ ይህን ቃል አምኖታል
ኧረ እንዴት ይሆናል እህ ብዬ አልጠራጠር ኦሆ
እግዚአብሔር ከሰጠኝ ተራራማውን አገር
አዬ ተራራማውን አገር
ፈርቼ አልመለስም እህ ረጃጅሞቹን ኦሆ
እገጥማቸዋለሁ ጠርቼው አምላኬን
አሄ ጠርቼው አምላኬን
አዝማች · Chorus
እልፍ በል ያለኝ ጌታ ከእኔ ጋር ነው
መንገዴን ጀምሬ እንዴት እመለሳለሁ
ከእኔ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል
ልቤም ላይደነግጥ ይህን ቃል አምኖታል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ