ትላንት ተብሎ
Telant Tebelo
2006 · ትራክ 7 · 5:59 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ትላንት ተብሎ ዛሬ ሊጠራ
አሳልፎት ነው እግዚአብሔር ሁሉን በተራ
አምላኬን እንዲህ በሉልኝ ሥራህ ግሩም ነው
እርሱ በሰራልኝ ተዓምራት/ቀናቶች እኔ ኖራለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ልዩነት አምጥቶ ሌሊቱ
ለጠላቴ ሆነ ውድቀቱ
ሊያጠፋኝ ነበረ ምኞቱ
እንዲሁ ደከመ በከንቱ
እኔማ አምልጫለሁ ወጥመዴ ተሰብሮ
ጠላቴ ላይደግም አንድ ጊዜ ጥሎ
እኔማ አምልጫለሁ ወጥመዴ ተሰብሮ
ጠላቴ ላይደግም ከእግሬ በታች ጥሎ
ይጨምራል ገና ሙሉ ቀን እስኪሆን (፪x)
የአምላኬን ተዓምራት አያለሁ ማዳኑን (፪x)
ለነገም ለዛሬ ምላሽ አለው ጌታ
በጭራሽ አልወርድም እኔ ከአየልኝ ከፍታ
አዝማች · Chorus
ትላንት ተብሎ ዛሬ ሊጠራ
አሳልፎት ነው እግዚአብሔር ሁሉን በተራ
አምላኬን እንዲህ በሉልኝ ሥራህ ግሩም ነው
እርሱ በሰራልኝ ተዓምራት/ቀናቶች እኔ ኖራለሁ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ደሙ በመቃኔ በጉበኔ ላይ ነው (፪x)
ቀኑ ክፉ ቢሆን ነግሬው አልፋለሁ (፪x)
በሞት ጥላ ብሄድ መቼ ያስፈራኛል
ሰባሪው እግዚአብሔር ከፊቴ ቀድሞ ወጥቶልኛል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ