ነገር ሁሉ ለበጐ
Neger Hulu Lebego
2006 · ትራክ 4 · 6:51 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢሄ ለምን ሆነ አልልም (አልልም)
ስንፍናን በአምላኬ አላወራም (እኔ አላወራም)
እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ነገር ሁሉ ለበጐ (ለበጐ/ለበጐ ነው) (፪x)
ኢሄ ለምን ሆነ አልልም (አልልም)
ስንፍናን በአምላኬ አላወራም (እኔ አላወራም)
እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ነገር ሁሉ ለበጐ (ለበጐ ነው/ለበጐ) (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ያሰብኩትን ባላገኝ የተመኘሁትን
ምላሼን ባይሰጠኝ የፍለጋዬን
ሁሉን ሰጥቶ ለእኔ እኔን ላያጣኝ
አውቆ ነው እግዚአብሔር የከለከለኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢሄ ለምን ሆነ አልልም (አልልም)
ስንፍናን በአምላኬ አላወራም (እኔ አላወራም)
እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ነገር ሁሉ ለበጐ (ለበጐ/ለበጐ ነው) (፪x)
ኢሄ ለምን ሆነ አልልም (አልልም)
ስንፍናን በአምላኬ አላወራም (እኔ አላወራም)
እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ነገር ሁሉ ለበጐ (ለበጐ ነው/ለበጐ) (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱ እንደራሱ ነው እንደ አፉ ቃል
እኔ እንደፈለኩት መቼ ይሆናል
አስቀድሞ ያውቃል የሚረባኝን
ከፊቴ ወሰደው የዓይን አምሮቴን
አዝማች · Chorus
ኢሄ ለምን ሆነ አልልም (አልልም)
ስንፍናን በአምላኬ አላወራም (እኔ አላወራም)
እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ነገር ሁሉ ለበጐ (ለበጐ/ለበጐ ነው) (፪x)
ኢሄ ለምን ሆነ አልልም (አልልም)
ስንፍናን በአምላኬ አላወራም (እኔ አላወራም)
እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ነገር ሁሉ ለበጐ (ለበጐ ነው/ለበጐ) (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተኑ መጠበቅ ይሻላል
ወዲህ ወዲያ ማለቱ ምን ይረባል
ከአንተ ጋር ተስማምቶ መኖር ነው
ነገር ሁሉ ይሆናል በጊዜው
ሁሉም ነገር ይሆናል በጊዜው
አንተኑ መጠበቅ ይሻላል
ወዲህ ወዲያ ማለቱ ምን ይረባል
ከአንተ ጋር ተስማምቶ መኖር ነው
ነገር ሁሉ ይሆናል በጊዜው
ሁሉም ነገር ይሆናል በጊዜው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ