ትዝ ይለኛል
Tez Yelegnal
2006 · ትራክ 3 · 5:04 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትላንትን ሳስበው በዛሬ ላይ ሆኜ
ስንቱን አልፊያለሁ እኔ አንተን መክሬ (፪x)
ምንድን ነው ስል እንደዚህ ያቆመኝ
ምህረትህ ነው ለእኔ ትዝ የሚለኝ
አባት መሆንህ ነው ለእኔ ትዝ የሚለኝ
አዝማች · Chorus
ትዝ ይለኛል ስለ እኔ ያነባ በመስቀል ላይ የጣለ
ትዝ ይለኛል አንተ ሞትህ ለእኔ እኔን ልታኖር
ትዝ ይለኛል መነሻ ሳይኖረኝ እንዲህ የወደድከኝ
ትዝ ይለኛል በፍቅርህ እኮ ነው ኧረ እኔን ያስጣለኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለካስ ልክ ነበር ስትነግረኝም ያኔ
ዛሬ ደርሼበት አይቻለሁ በዓይኔ (፪x)
አላማርርህም ሳስብ መፈጠሬን
ለእኔ ተስማምቶኛል ከአንተ ጋር መኖሬ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትዝ ይለኛል ስለ እኔ ያነባ በመስቀል ላይ የጣለ
ትዝ ይለኛል አንተ ሞትህ ለእኔ እኔን ልታኖር
ትዝ ይለኛል መነሻ ሳይኖረኝ እንዲህ የወደድከኝ
ትዝ ይለኛል በፍቅርህ እኮ ነው ኧረ እኔን ያስጣለኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ትዝ ይለኛል ርህሩሁን አብርደህ በረድ ስታኖረኝ
ትዝ ይለኛል እንደ አባት ሆነህ መክረህ ያሳደከኝ
ትዝ ይለኛል ያንን ምድረበዳ በአንተ ያለፍኩበት
ትዝ ይለኛል በሕይወት ያኖረኝ የምህረትህ ብዛት
ነፋሱም ሳይነፍስ አይኖርም ደመና
በስብከት ሞኝነት ተቀበልኩህና (፪x)
ስለ አንተ ሲወራ ከሩቁ ሰምቼ
ቀርቤ አየሁኝ ማዳንን በዓይኖቼ
አባት መሆንህን አየሁኝ በዓይኖቼ
ቁጥር 4 · Verse 4
ትዝ ይለኛል ርህሩሁን አብርደህ በረድ ስታኖረኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ትዝ ይለኛል እንደ አባት ሆነህ መክረህ ያሳደከኝ
ትዝ ይለኛል ያንን ምድረበዳ በአንተ ያለፍኩበት
ትዝ ይለኛል በሕይወት ያኖረኝ የምህረትህ ብዛት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ