አንተ ታማኝ ነህ
Ante Tamagn Neh
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማለዳ ማለዳ ምህረትህ አዲስ ነው
ታማኝነትህም እጅጉን ብዙ ነው (፪x)
ማለዳ ማለዳ ምህረትህ አዲስ ነው
ታማኝነትህም እጅጉን ብዙ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጉልበት ሲዝል አቅም ጠፍቶ አይዞህ ባይ ሲታጣ
ማን እንዳንተ የኔ ጌታ አለሁ ባይ መከታ
ቢደገፉት እሚያኮራ ቢታመኑት ታማኝ
አይገኝም ካንተ በቀር በምድርም በሰማይ
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጠላት ቢዋዥ በኃይልህ ላይ ትርፉ ድካሙ ነው
ያልከው አይቀር ይፈጸማል ምክርህ የጸና ነው
ትላንትናን እንደሰራህ ዛሬም ትሰራለህ
ክንድህ አይዝል አስተማማኝ ሁልጊዜም ታማኝ ነህ
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተን ይዞ ማን አፈረ ካንተ የተጠጋ
አድነኸው አማረበት ከጠላት መንጋጋ
ታሪክ መስራት ልማድህ ነው ክንድህ አይታክትም
እርስትህን አሳልፈህ ለጠላት አትሰጥም
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ማለዳ ማለዳ ምህረትህ አዲስ ነው
ታማኝነትህም እጅጉን ብዙ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
በዙሪያዬ ጋሻ የእሳት ቅጥር ሆነ
ከጥፋት ማምለጫ ኢየሱስ አለቴ ነህ
በለመለመ መስክ መምራት ስታውቅበት
የዘላለም ብርሃን ቀን ለጨለመበት
የዘላለም ብርሃን ነህ የዘላለም ብርሃን (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ