Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከልኩ አያልፍም

Keliku Ayalfim

ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

"ወይ የምታልፍ ብሎ ያለወትሮው ሞልቶ ዮርዳኖስ ቢፎክር ቢቆምም ከፊቴ

በዳር አስከ ክብር እሄዳለሁ አልፈራም ጌታ ነው ጉልበቴ

ረግጬው አልፋለሁ ጌታ ነው ጉልበቴ ፣ ኢየሱስ ነው ጉልበቴ"

ቢጮህም አያሸንፍም ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም

የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ለጠላት ዕድል አልሰጠው (፪x)

ለጠላት ዕድል አልሰጠው (፬x)

ሰባት እጥፍ ብያነድ ጠላቴ እሳቱን አብዝቶ

ከከፍታዬ ላይ አልወርድም ስፍራ አለቅም ከቶ

የመቆሜ ሚስጥር ጌታ እንጂ አይደለም ሁኔታ

የታመንኩበትን አውቃለሁ አንደማይረታ (፪x)

ቢጮህም አያሸንፍም ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም

የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ለጠላት ዕድል አልሰጠው (፪x)

ለጠላት ዕድል አልሰጠው (፬x)

ጠላቴን ከፊቴ አውጥቶት አጥፋው ብሎ አዞኛል

አስጨናቂውን ዘንግ ጌታ ፈጥኖ ሰብሮልኛል

የከፍተኛነቴ ሰይፍ ብቃቴም እርሱ ነው

አትፍራ ሰላለኝ አልፈራም ጌታ ከኔ ጋር ነው (፪x)

ጌታ ከኔ ጋር ነው(፬x)

ቢጮህም አያሸንፍም ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም

የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ለጠላት ዕድል አልሰጠው (፪x)

ለጠላት ዕድል አልሰጠው (፬x)

ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ አስደንቆኛል (፪x)

እግዚአብሔር ስራዬን ሁሉ ሰርቶልናል (፪x)

ላመስግነው አንጂ ስሙን በዝማሬ (፪x)

ለጠላቴ ሃዘን የድል ቀን ነው ዛሬ ፣ የድል ቀን ነው ዛሬ (፪x)

ቢጮህም አያሸንፍም ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም

የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ለጠላት ዕድል አልሰጠው (፪x)

ለጠላት ዕድል አልሰጠው (፱x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ