የውዴ እጆቹ
Yewedie Ejochu
ትራክ 7 · 5:10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ዳሰሱኝ የውዴ እጆቹ
ጎበኙን መልካም አይኖቹ
ተዳሰስኩ ተለውጫለሁ
አምላኬን አመልከዋለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ይህ አምላኬ ነዉ አመልከዋለሁ
በምህረቱም ደስ እሰኛለሁ
እኔ የእርሱ ነኝና ያስብልኛል
ደጋግ እጆቹም ይዳስሱኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
ዳሰሱኝ የውዴ እጆቹ
ጎበኙን መልካም አይኖቹ
ተዳሰስኩ ተለውጫለሁ
አምላኬን አመልከዋለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያማምነው አምላክ የምደገፈው
ከሁሉም በላይ አለኝ የምለው
ላፍታ እንኳን አንዴም ጀርባ አልሰጠኝም
የፍቅር አይኑ አልተለየኝም (፪x)
አዝማች · Chorus
ዳሰሱኝ የውዴ እጆቹ
ጎበኙን መልካም አይኖቹ
ተዳሰስኩ ተለውጫለሁ
አምላኬን አመልከዋለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ