ልነሳ ላመስግን
Lenesa Lamesgin
ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በቃልህ ትእዛዝ በስልጣንህ በትር
ሁሉን ትገዛለህ ላንተ ይሁን ክብር
ከክብር ጋር ስፍራን በቀኝህ ሰጠኸኝ
ምን ቢለፋ ቢጥር ጠላቴ አያገኘኝ
አዝማች · Chorus
ልነሳ ላመስግን ዝቅ ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር
ልሰዋ ምስጋና ክብር የሚገባህ ነህና (፪x)
ክብር የሚገባህ ነህና (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሚታየው አልለውጥህም
በሁኔታ አልገምትህም
ቢመሽም ቢነጋም አውቃለሁ
አንተን ለማመስገን እቆማለሁ ፪x
አዝማች · Chorus
ልነሳ ላመስግን ዝቅ ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር
ልሰዋ ምስጋና ክብር የሚገባህ ነህና (፪x)
ክብር የሚገባህ ነህና (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዘመኔን በክብርህ አስዋብከው ከአውሬና ከተኩላው አድነህ
ከክብር ወደ ክብር መራኸኝ በእጅህ እጄን ይዘህ
ታሪኬ ሆንክልኝ ትምክቴ ትርጉም ለሕይወቴ
አመሰግናለሁ ከፍ በል ኢየሱስ መድኃኒቴ (፪x)
አዝማች · Chorus
ልነሳ ላመስግን ዝቅ ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር
ልሰዋ ምስጋና ክብር የሚገባህ ነህና (፪x)
ክብር የሚገባህ ነህና (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደ ባለማዕረግ ተቀብለኸኛል
እቅፍህ ይደላል ተመችተኸኛል
የሕይወቴ እርካታ አንተ ከሆንክልኝ
ዓይኔ ሌላ አያይም ምን ሊፈይድልኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ልነሳ ላመስግን ዝቅ ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር
ልሰዋ ምስጋና ክብር የሚገባህ ነህና (፪x)
ክብር የሚገባህ ነህና (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ