በእርሱ ነው
Bersu New
ትራክ 11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው
የለም አንዳች ከኔ ብዬ ምለው
በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው
በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጽድቅ ነው ለኔስ ጌታዬ ጽድቅ ሆኖ የተቆጠረልኝ
ጠላቴን ድባቅ የመታው ከእግሬ ስር ፈጥኖ የጣለልኝ
ላክብረው ሥሙን በዜማ ቅኔዬን አሰካክቼ
አልችልም ዝም ለማለት ልባርከው እጄን አንስቼ
አዝማች · Chorus
ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው
የለም አንዳች ከኔ ብዬ ምለው
በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው
በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተዓምርን ሰርቶ ያዳነኝ ሞቴንም በሞት የሻረው
ትንሳዔን ለኔ ያወጀ ታሪኬን የለዋወጠው
ምስኪኑን ከትቢያ አንስቶ በድል ላይ ድል የሚሰጠው
እንዲህ ነው የታመንኩበት አምላኬ ብዬ የምለው
አዝማች · Chorus
ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው
የለም አንዳች ከኔ ብዬ ምለው
በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው
በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የእግዚአብሔር ምህረቱ ገንኖልኝ በላዬ
ጨለማዬም በራ ቆምኩኝ ቀና ብዬ (፪x)
ተከፋፈተልኝ የሰማዩም ደጃፍ
አምላኬ ሲረዳኝ አየሁ አዲስ ምዕራፍ (፬x)
አዝማች · Chorus
ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው
የለም አንዳች ከኔ ብዬ ምለው
በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው
በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ