ገናና ነህና
Genana Nehina
ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በአዲስ በአዲስ ቅኔ ባማረ ምስጋና (፪x)
እሰዋልሃለሁ ይገባሃልና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ገናና ገናና ነህና (፬x)
እታመንሃለሁ ትምክህቴ ነህ ለኔ
መልካምነት ህን አይቻለሁ ባይኔ
የምስጋናዬም ቃል ይውጣና ይሰማ
ገና እጨምራለሁ ይህ ካረካህማ
አዝማች · Chorus
በአዲስ በአዲስ ቅኔ ባማረ ምስጋና (፪x)
እሰዋልሃለሁ ይገባሃልና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ገናና ገናና ነህና (፬x)
ሞገሴ ነህ ጌታዬ በጥላህ አርፌአለሁ
ላመልክህ ይገባኛል ፍቅርህን ቀምሻለሁ
ኃያል ነህ ክንደ ብርቱ ማን እንተን ይጋፋና
ዙፋንህ የጸና ነው ልዩ ነህ ባለዝና (፪x)
አዝማች · Chorus
በአዲስ በአዲስ ቅኔ ባማረ ምስጋና (፪x)
እሰዋልሃለሁ ይገባሃልና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አምላኬ አምላኬ ነህና (፬x)
አንተን ይዤ አላፈርኩም አታሳፍርምና
ሁሉን አሻግረኸኛል ከበህ ከፊት ከኋላ
እግሬን በከፍታ ላይ አጽንተህ አቁመሃል
ገናና ነህ እያልኩኝ ባመልክህ ያንስብሃል (፪x)
ገናና ገናና ነህና (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ