Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ህልሜ ሰምሯል

Helmie Semrual

ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በእቅፍህ መሃል ስፍራን ሰጠኸኝ ተደላድዬ

እፎይ ብያለሁ አንተን አግኝቼ ክበር ጌታዬ

እንዳልታወክ በቀኜ አለህ ውስጤ መች ሰግቶ

ልቤም ይጣራል ኢየሱስ እያለ በፍቅርህ ነዶ (፪x)

(ኢየሱስ) የሕይወቴ ትርጉም (ኢየሱስ) የሆንክልኝ ፍቺ (፪x)

(ኢየሱስ) ክብርን አይቻለሁ (ኢየሱስ) እኔስ በአንተ እጅ (፪x)

ሁሉን ቻይ አምላክ ወረት የማታውቅ እሩህሩህ ጌታ

ፍቅርህ ማረከኝ የአንተ እንድሆን ልቤም ተረታ

ሌላ አይገዛንም ከአንተ በስተቀር በምድር ያለው

ሁሉ የሞላህ ባለ ፀጋ አምላክ አንተን ይዣለሁ (፪x)

ክበርልኝ (፫x)

አላየሁም ከአንተ የሚበልጥብኝ

ንገስልኝ (፫x)

አልሰማሁም ከአንተ የሚበልጥብኝ

አላየሁም ከአንተ የምበልጥብኝ

አልሰማሁም ከአንተ የምበልጥብኝ (፪x)

ስትሾም ስትሸልም (አቤት ስታውቅበት)

ደርሰህ ብርሃን (ስትሆን ቀን ለጨለመበት)

ስታውቅበት ማበጃጀት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ