Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እልፍ ቃል በኖረኝ

Elf Qal Benoregn

ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኢየሱስ አለቴ ነህ ተደግፌሃለሁ

አንተ ሁሉን ቻይ ነህ በጥላህ አርፋለሁ

ከቶ አልጨነቅም ለነገዬ ብዬ

ሁሉን የምትሆን ስላለህ ጌታዬ

ሁሉን የምትሆን ስላለህ ጌታዬ (፪x)

እልፍ ቃል ቢኖረኝ አንተን ማሞገሻ (፪x)

አመስግኜ አልጠግብም እስከመጨረሻ (፪x)

ባለ ብዙ ምህረት ባለ ብዙ ፀጋ

ማንስ ወድቆ ቀርቷል አንተን የተጠጋ

በጊዜው የምትደርስ ተቀድመህ አታውቅም

ታማኝ ነህ አምላኬ እንደ ሰው አትዋሽም

ታማኝ ነህ ኢየሱሴ እንደ ሰው አትዋሽም (፪x)

እልፍ ቃል ቢኖረኝ አንተን ማሞገሻ (፪x)

አመስግኜ አልጠግብም እስከመጨረሻ (፪x)

ይገርመኛል ይደንቀኛል

ጌታ ምህረትህ ለኔ ያለህ አላማ

ፍፁም ደግነትህ (፪x)

ልትመለክ የሚገባህ

ልትወደስ የሚገባህ (፪x)

ገናና ነህ የሁሉ የበላይ

ከፍ በል በምድርም በሰማይ (፪x)

ብንሰግድልህ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ