Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አስታዋሼ

Astawashie

2010 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰው የረሳኝን አስታወስከኝ

ከአመድ ከትቢያ ያነሳኀኝ

እኔም ስላየሁ ክንድህን

ጌታ ደራሽ ነህ ልበልህ (፪x)

(ደራሽ ነህ) ምድረ በዳውን ፤ (ደራሽ ነህ) ያሳለፍከኝ

(ደራሽ ነህ) ምንጭን አፍልቀህ አጠጣኀኝ

(ደራሽ ነህ) አንዴ ጠጥቼ ፤ (ደራሽ ነህ) እንዳልጠማ

(ደራሽ ነህ) ሕይወት ሆንክልኝ በሞት ከተማ

(ደራሽ ነህ) ጌታ ፤ (ደራሽ ነህ) ለእኔ

(ደራሽ ነህ) ውዴ ፤ ደራሽ ነህ ለእኔ

ቃል ሲወጣ ከሰማይ ማን ይቆማል ደጃፉ ላይ

(ማን ይቆማል ሄ ማን ይቆማል ደጃፉ ላይ)

በአንዲት ጀምበር ደረስክና አፌን ሞላህ በምሥጋና

(ማን ይቆማል ሄ ማን ይቆማል)

እንዳለፈው ታለፈ አበሳዬ ተረሳ

(ማን ይቆማል ሄ ማን ይቆማል ደጃፉ ላይ)

እኔም ዛሬ ወግ ደረሰኝ የአስታዋሼን ስሙን ላንሳ

(ማን ይቆማል ሄ ማን ይቆማል)

አስታዋሼ የእኔ ኧረኛ

ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ

አስታዋሼ የእኔ ዳኛ

ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ (፪x)

ሰው የረሳኝን አስታወስከኝ

ከአመድ ከትቢያ ያነሳኀኝ

እኔም ስላየሁ ክንድህን

ጌታ ደራሽ ነህ ልበልህ (፪x)

(ደራሽ ነህ) ምድረ በዳውን ፤ (ደራሽ ነህ) ያሳለፍከኝ

(ደራሽ ነህ) ምንጭን አፍልቀህ አጠጣኀኝ

(ደራሽ ነህ) አንዴ ጠጥቼ ፤ (ደራሽ ነህ) እንዳልጠማ

(ደራሽ ነህ) ሕይወት ሆንክልኝ በሞት ከተማ

(ደራሽ ነህ) ጌታ ፤ (ደራሽ ነህ) ለእኔ

(ደራሽ ነህ) ውዴ ፤ ደራሽ ነህ ለእኔ

ኢየሱሴ ባታየኝ ማን ነበረ የሚያየኝ

(ማን ነበረ ቆይ ማን ነበረ የሚያየኝ)

ግራ ገብቶኝ ስንገላታ ደረስክልኝ የእኔ ጌታ

(ማን ነበረ ሄ ማን ነበረ)

እነዛ እጆች ይባረኩ እኔን አቅፈው ያሳደጉ

(ማን ነበረ ቆይ ማን ነበረ የሚያየኝ)

አደረግከኝ ሽቅርቅር ጠላት ይፈር ያቀርቅር

(ማን ነበረ ሄ ማን ነበረ)

አስታዋሼ የእኔ እረኛ

ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ

አስታዋሼ የእኔ ዳኛ

ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ (፪x)

እንዴት አስታወስከው ያንን ሰው (፪x)

እንዴት አስታወስከው ያንን ሰው (፪x)

እንዴት አስታወስከው ያንን ሰው (፪x)

እንዴት አስታወስከው ያንን ሰው (፪x)

አስታዋሼ የእኔ ኧረኛ

ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ

አስታዋሼ የእኔ ዳኛ

ሰው ሲረሳኝ አሰብከኛ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ