አልችልበትም
Alchelebetem
2010 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስለማልችል ያለ አንተ መኖር
አትሂድብኝ ባክህ ጌታ ሆይ
እኔስ ያለ አንተ አልችልምና
ችላ አትበለኝ ክብሬን ክብሬ ነህና
አዝማች · Chorus
አልችልበትም እኔስ
አይሆንልኝም እኔስ
ቁጥር 2 · Verse 2
ያላንተ መኖር (፪x)
ዓይኔን በእጄ አልወጋም የጠራኝን ትቼ
እንዴት ነው ምኖረው ከአንተ ተለይቼ
ሌላው ሚመካበት አለው ብዙ ነገር
ለእኔ ግን አንተ ነህ የመኖሬ ትርጉም
አዝማች · Chorus
አልችልበትም እኔስ
አይሆንልኝም እኔስ
ቁጥር 3 · Verse 3
ያለአንተ መኖር
ሲከብደኝ ብቸኝነቴ ሳዝን ስተክዝ በቤቲት
ቅዱሱን መንፈስ አልኩኝ እባክህ አትሂድብኝ
የሰው ጥማቱ ሌላ ነው
የኤኔ ግን አንድ ብቻ ነው
ያላንተ መኖር አልችልም
ለአፍታ እንኳን አትተወኝ
ስለማልችል ያለ አንተ መኖር
አትሂድብኝ ባክህ ጌታ ሆይ
እኔስ ያለ አንተ አልችልምና
ችላ አትበለኝ ክብሬን ክብሬ ነህና
ሳኦል ምን ነክቶት ከሰረ
ለሥጋው ምቾት ስለአደረ
አጥፋልኝ ብለህ ስትልከው
ያማረውን ለኤራሱ አስቀረው
በሚያልፈው ነገር ተታሎ
በድፍረት ሲጓዝ አይ ብሎ
ድምጽህን ንቆ ሲወጣ
መንፈስህ ሸሽቶ ተቀጣ
አጥፋልኝ ያልከውን አጠፋዋለሁኝ
ሰዋልኝ ያልከውን እሰዋዋለሁኝ
ዝክሩን ከምድር ላይ
መንግሥቱን አፍርሼ
አስደስትሃለሁኝ ቃልህን ጠብቄ
አዝማች · Chorus
አልችልበትም እኔስ
አይሆንልኝም እኔስ
ቁጥር 4 · Verse 4
ያላንተ መኖር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ