ከአንተ ጋር
Keante Gar
2010 · ትራክ 3 · 6:06 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከአንተ ጋር ልኑር አንተ ጋር ከአንተ ጋር
ኢየሱስ ልኑር አንተ ጋር ከአንተ ጋር
ያለ አንተ አይሆንልኝም ከአንተ ጋር
ብቻዬን አያምርብኝ ከአንተ ጋር
ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር
ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በንጉሥ ጮማ ከኖሩ ቆሎ ቆርጥመው ያደሩ
አስር እጅ አማረባቸው ከአንተ ጋራ የወገኑ
በምድር ተጨምጭቦልኝ በሰማይ ከምታፍርብኝ
ይቅርብኝ ሁሉም ይቅር ከአንተ ጋራ ብቻ ልኑር
መራብን አውቃለሁ መጥገብን
ማግኘትን አውቃለሁ ማጣትን
እኔ ማይሆንልኝ ማያምርብኝ
ያላንተ መኖር ነው የታውቅክልኝ
ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር
ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር (፪x)
አዝማች · Chorus
ከአንተ ጋር ልኑር አንተ ጋር ከአንተ ጋር
ኢየሱስ ልኑር አንተ ጋር ከአንተ ጋር
ያለ አንተ አይሆንልኝም ከአንተ ጋር
ብቻዬን አያምርብኝ ከአንተ ጋር
ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር
ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር
ቁጥር 2 · Verse 2
ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር
ባልጠጣ ያረካኛል ከአንተ ጋር
ቢቃጠል ወጣትነቴ ቢነድም ለአንተ ጉልበቴ
ቢቀናም ክፉ ጠላቴ ለአንተ ብቻ ነው አባቴ
የሰው ልጅ ዕድሜ ሰንቃላ ሰማንያ አመት የማይሞላ
ድካም ነው ከዚያ በኋላ አልሆንም እኔስ ተላላ
ሺህ ዓመት አልኖርም በምድር
ኧረ እንደእንፋሎት ነው የሰው ልጅ ዘመን
በቃ ለአንተ ክብር ልኑርና
ዘመኔን ጨርሰው ጌታ ቀድስና
ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር
ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር (፪x)
ሙሴ አይቶ ብድራቱን የልጅ ልጅ ንግስናውን
ንቆታል ለእግዚአብሔር ብሎ ዋጋውን ክብሩን ተምኖ
ኧረ ለእኔ ትልቅ እድል ነው ከአንተ ጋር ብዬ ምኖረው
እንኳን አገልጋይ ሆኜ ይበቃል ባሪያ መባሌ
የእኔ መጨረሻ ጥግ እርካታዬ
መገኘትህ ሲኖር በቤት በጓዳዬ
ያን ጊዜ በፍፁም ልቤ ኧረካለሁ
ፊትህን እያየሁ ሁልጊዜ እጠግባለሁ
ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር
ባልበላ እጠግባለሁ ከአንተ ጋር
ይሄ ልቤ ተመኝቶሃል ልኑር ከአንተ ጋር
ባልጠጣ ያረካኛል ከአንተ ጋር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ