ትርፌማ ቅባት ነው
Terfiema Qebat New
2010 · ትራክ 7 · 5:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሥምህ በአፌ ላይ ይጣፍጠኛል
ሁሌ ስጠራው ደስ ደስ ይለኛል
የትኛው ሥም ነው የተወደደው
ጠዋት ተወርቶ ማታ የሚወርደው
እንዳየነው
የእኔ ኢየሱስ ግን ሥሙ ይለያል
ሁሌ ስጠራው ደስ ደስ ይለኛል
ጠረነ ልዩ ማዕዛ ያለው
የአባትዬ ሥም ልክ እንደ ማር ነው
እንደ ማር
አዝማች · Chorus
እንደ ማር ኧረ እንደ ማር (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔስ ቆርጫለሁ ለጌታ ዘንድሮ
ሕይወት ተገለጠ በራልኝ በቶሎ
ዋጋዬን ተምኜ ስለወጣሁኝ
እመቅደሱ ደጃፍ ወስዳችሁ ጣሉኝ
ትርፌማ ቅባት ነው ቅባት በመንገዴ
ያገኘኛል አልኩኝ ያየኛል አባቴ
ዋጋዬን ተምኜው ስለወጣሁኝ
እመቅደሱ ደጃፍ ወስዳችሁ ጣሉኝ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አሄ ኦሆ
አርዶ የወጣ ሰው ከቶ አይመለስም
ጌልጌላ ተነስቶ ቤቴል ላይ አይቆምም
እያሪኮን አልፎ ዮርዳኖስ ይዘልቃል
እጥፍ መንፈስ ይዞ በክብር ይመለሳል
በኤልያስ እጅ ላይ ውኃ የሚያፈሰው
አስራ ሁለት ጥማድ በሬ አረደው
በሕያው ልብሱ ምን አለ የተከተለው
ሞኝ ሆኖ አይደለም ክብር አይቶ ነው
ቅባት አይቶ ነው ክብር አይቶ ነው
ጌልጌላ ሸለፈትክ የተገረዘው
ቤቴል የእግዚአብሔር ቤት የተጸለየው
እያሪኮም ይናድ በጩኸት ይፍረስ
ዮርዳኖስ ልጠመቅ በመንፈስ ቅዱስ
አባናና ፋርፋን አልል እንደ ሰው
ዮርዳኖስ ይበልጣል የደፈረሰው
ብቅ ትልቅ ብዬል ከለምጽ እነጻለሁ
አንተ ያልከኝ ቦታ ፈውስ አገኛለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
መዳን አገኛለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ዘመኔ እንደ ሻማ እንደ ጧፍ ቢነድ
ያንስበታል እንጂ መች ይበዛበት
እርሱማ ተዋርዶ በሞቱ አክብሮኝ
ለኢየሱሴ ኖሬ እስቲ ይለይልኝ
አሸፈተው ልቤን ኢየሱስን ወዶ
የሠማይ አስባለኝ የምድሩን አስንቆ
ልቤ ትዝታዬም እርሱ ጋር ቀረና
ሁሉንም አሳቀኝ የእርሱ በለጠና
ክብር በለጠና ቅባት በለጠና
ሞኝ ነህ ይሉኛል የታል ሞኝነቴ
አተረፈኩኝ እንጂ ምንድን ነው ጉዳቴ
ኢየሱስን ይዤ እኔስ አትርፊያለሁ
ምድር ተቀምጬ ቤቴ በሠማይ ነው
ይኸውልህ ልቤን እንካ ውሰደው
አንተ ጋር ይቀመጥ የእኔ ከንቱ ነው
ሁሉንም ሰብስቤ ለአንተ ሰጠሁና
አንተን አንተን አልኩኝ የአንተ በለጠና
መንፈስ በለጠና ቅባት በለጠና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ