ካልባረከኝ
Kalbarekegn
2010 · ትራክ 12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በረከት ፍለጋን ስንከራተት
እንዲያው በከንቱ አይ ስዋትት
ዛሬ ግን ገብቶኝ መጥቻለሁ
አንተን ከአገኘሁ ምን እሻለሁ
አዝማች · Chorus
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ስሜን ቀይረህ ካልቀባኀኝ
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ልጄ ነህ ብለህ ካለወጥከኝ
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሓሩሩ ኩሩ አቃጠለኝ
ደሞዜን ስንቴ ቀየረብኝ
ሽቅብ ስወጣ ቁልቁል ስወርድ
ዘመኔን ፈጀሁ በላባ ቤት
ቆይ ምን ያደርጋል ሃብት ቢበዛ
አንተ ከሌለህ ካልሆንከኝ ቤዛ
ሌሊቱ አቅላልቷል ሊነጋብኝ
እኔ አለቅህም ካልባረከኝ
ጌታ አድነኝ ለውጠኝ
ማለቴን አልተውም እስክትለውጠኝ
ጌታ አድነኝ ለውጠኝ
ጸሎቴን አልተውም እስክትለውጠኝ
በረከት ፍለጋን ስንከራተት
እንዲያው በከንቱ አይ ስዋትት
ዛሬ ግን ገብቶኝ መጥቻለሁ
አንተን ከአገኘሁ ወርሻለሁ???
አዝማች · Chorus
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ስሜን ቀይረህ ካልቀባኀኝ
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ልጄ ነህ ብለህ ካለወጥከኝ
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የቅድስናን የጽድቅን ኑሮ
መኖር ፈልጌ ከአምናው ዘንድሮ
አመታት ዘመን ወሰደብኝ
መቼ ነው መጥተህ ምትቀይረኝ
እኔ አልፈልግም እንደዚህ ኑሮ
ተራራ መዞር አመታት ቆጥሮ
እስቲ አንድ እርምጃ ፈቀቅ አርገኝ
በክብርህ ልኑር አሳርፈኝ
ጌታ አድነኝ ለውጠኝ
ማለቴን አልተውም እስክትለውጠኝ
ጌታ አድነኝ ለውጠኝ
ጸሎቴን አልተውም እስክትለውጠኝ
አዝማች · Chorus
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ስሜን ቀይረህ ካልቀባኀኝ
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ልጄ ነህ ብለህ ካለወጥከኝ
ካልባረከኝ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ አልተውህም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ