መልሰኝ
Melesegn
2010 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እረጅሙን ጐዳና በጽድቅ እንዳልሄድኩኝ
አንተን እንዳላሳዝን ፊትህ እንደማልኩኝ
ዛሬ ምነው ጠፋኝ አቅም አጠረኝኝ
እኔ ነኝ ጥፋተኛ እኔን እኔን ማረኝ
ዕንቁዬን ሜዳ ጥዬው ብቻዬን ቀረሁኝ
ጌታ ሆይ መልሰኝ ምህረት አድርግልኝ
አዝማች · Chorus
መልሰኝ ወደድሮዬ ፣ መልሰኝ ወዳስተማርከኝ
መልሰኝ ወደጓዳዬ ፣ መልሰኝ ወደነገርከኝ
አንተን ተጣልቼ እንዴት እሆናለሁ
ከአንተ ተስማምቼ እኔስ እኖራለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ስታበይ ገሥጸኝ ሳጠፋ ቅጣኝ
መንፈስህን ከእኔ አትውሰድብኝ
አንተ ዝም ካልከኝ ምንስ ይውጠኛል
የአንተ ዝምታ እኮ አፍ አለው ያወራል
ብቻ ይሁን እንጂ የነገርከኝ ኢየሱስ ያልከኝ
እኔስ ከሃሳብህ ጋር እስማማለሁ ይሁን እንዳልከኝ (፪x)
ብዙ የለፋሁበት ያከማቸሁት ሃብቴ
ከእጄ ላይ ተበተነ ሳላውቀው ከጥማቴ
የተቀደስኩለት ከዳኝ ማንነቴ
አወይ አለመታዘዝ አሻፈረኝ ማለቴ
አይረባህም ስትለኝ አንተን አለመስማቴ
ዛሬ ግን ገብቶኛል አድሰኝ አባቴ
አዝማች · Chorus
መልሰኝ ወደድሮዬ ፣ መልሰኝ ወዳስተማርከኝ
መልሰኝ ወደጓዳዬ ፣ መልሰኝ ወደነገርከኝ
አንተን ተጣልቼ እንዴት እሆናለሁ
ከአንተ ተስማምቼ እኔስ እኖራለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጴጥሮስ ሓዋርያው አልክድህም ያለው
ዶሮ ሳይጮህ በፊት ሶስት ጊዜ ነው የካደው
ነገር ግን ምህረትህ እጅግ ስለበዛ
አስበህ ለወጥከው ሰው አደረከው ጌታ
ብቻ ይሁን እንጂ የነገርከኝ ኢየሱስ ያልከኝ
እኔስ ከሃሳብህ ጋር እስማማለሁ ይሁን እንዳልከኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ