ክንዱ ነው
Kendu New
2010 · ትራክ 2 · 6:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ክንዱ ነው ታሪኬን የለዋወጠው
ጣቱ ነው ነገሬን የቀያየረው (፪x)
አይቻለሁ በአንተ
ሸለቆው ውኃ ሲሞላ
ጌታ ስትሆነኝ ከለላ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አንገት እንድደፋ እንዳቀረቅር
ከሰው በታችን ሆኜ ነበር ምኞቱ
ጠላቴማ ሰው ለማድረግ ከንቱ አወይ ልፋቱ
የማመልከው ጌታ እጄን ያዘኝ
እንደገና አነሳኝ ዳግም አቆመኝ
ማነው ማነው ማነው ኧረ ማነው ማነው
ማነው ማነው ማነው እኮ ማነው ማነው
እሃሃሃ እግዚአብሔር እኮ ነው
ለእኔ የደረሰው (፪x)
አዝማች · Chorus
ክንዱ ነው ታሪኬን የለዋወጠው
ጣቱ ነው ነገሬን የቀያየረው (፪x)
አይቻለሁ በአንተ
ሸለቆው ውኃ ሲሞላ
ጌታ ስትሆነኝ ከለላ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በዚያ በጭንቅ ቀን በቁርጥ ጊዜ በመከራ ሰዓት
ከጐኔ የሚቆም አይዞህ የሚለኝ አጋዥ ባጣሁበት
የናዝሬቱ ኢየሱስ ወደ እኔ ሲመጣ
ጉልበቴም ከፍ አለልኝ አቅሜም በረታ
ማነው ማነው ማነው ኧረ ማነው ማነው
ማነው ማነው ማነው እኮ ማነው ማነው
እሃሃሃ እግዚአብሔር እኮ ነው
ለእኔ የደረሰው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ