አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ
Ategebie Honeh Tenafeqegnaleh
2014 · ትራክ 9 · 8:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በቀንና በሌሊት አንተን እፈልጋለሁ
ልቤም አንተን አለ
ደግሜ ደግሜ ኢየሱስ እልሃለሁ
ልቤ አንተን አለ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ
አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ
ውዴ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ
አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ
ቁጥር 2 · Verse 2
እፎይ ምልብህ ውስጤ ያለውን ሁሉ ተንፍሼ
በፊትህ ደስታ ሰላሜን ከልብስ ይልቅ ለብሼ
ልቤ ከናፍቆት አንተን ከማለት አይቆጠብም
ከአንተ ጋር መሆን ሚናፈቅ እንጂ አይጠገብም (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ
አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ
ውዴ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ
አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ነህና ነህና የሕይወቴ ትርጉም ኢየሱስ
ነህና ነህና የሕይወቴ ጣዕም ኢየሱስ (፪x)
ከገሃነም ጥርስ በአንተ መዳኔ በዝቶ ሳያንስ
በተከበበም መሃል ከተማ ሰላም ስትሆን
እረፍቴ እኮ ነህ ቅጥሬ እንዳይናድ በዓለም ሁካታ
አብዝቼ እላለሁ አብረኸኝ ሆነህ ናፈቅከኝ ጌታ (፪x)
ነህና ነህና የሕይወቴ ትርጉም ኢየሱስ
ነህና ነህና የሕይወቴ ጣዕም ኢየሱስ (፪x)
መሄድ መሄድ መሄድ ወዳንተ መገኛ
ለነፍሴ ነውና ርሃቧ
ቀና አልልም ሌሊት አልልም አብዝቼ እፈልግሃለሁ
የሕይወቴ ትርጉም የመኖሬ አላማ አንተ ጋር ነው ያለው
ኦ አንተን ጌታ እፈልግሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ
አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ
ውዴ ኢየሱስ ልቤ አንተን አለ
አጠገቤ ሆነህ ትናፍቀኛለህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ