ሕያው ምንጭ
Heyaw Mench
2014 · ትራክ 2 · 5:45 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሸቶናል የአንተ መገኘት ሸቶኛል
ሸቶኛል የአንተ ህልውና ሸቶኛል
እለመልማለሁ ብዙ አፈራለሁ
እለመልማለሁ ብዙ አፈራለሁ
አዝማች · Chorus
አልደርቅም አልደርቅም ሕያው ምንጭ
አንተ አለኸኝ ኢየሱስ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዛፍ እንኳ ቢቆረጥ
ደግሞ ሊያቆጠቁጥ አዲስን ቅርንጫፍ
ሊያበቅል ተስፋ አለው
ለፍጥረት የመታደስን
ይህ እንደገና ተስፋን ሰጠኸው
ለእኔማ አንተ ነህ ለእኔ የነፍሴ ተስፋ
የምትበልጥ ለማቆጥቆጤ ከውኃ ሸታ
የክፉ ምሳር ቆርጦ :ሊጥለኝ
እስከወዲያኛው ከአንተ ሊለየኝ
ስመታ ተንገዳግጄ
ስደርስ ወደታች ስቧጥጥ
ሲብስ ማቃሰት ሆኖብኝ አንዳች
ሲሸተኝ የመገኘትህ የአንተ መዓዛ
ቆማለሁ ዳግም በጽኑ ምህረት ሲበዛ (፪x)
አዝማች · Chorus
አልደርቅም አልደርቅም ሕያው ምንጭ
አንተ አለኸኝ ኢየሱስ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በድርቅ ዘመን ከቶ እንዳልሰጋ
ፍሬ ማፍራቴን ላይቆም አንዱ ጋር
እምነቴ አንተ ነህ መታመኛዬ
ሙቀት ሲመጣ ላይፈራው ልቤ
ከአንተ አጠገብ ተተክያለሁ
ስለዚህ ሕይወቴ ሁሌ ለምለም ነው (፪x)
ሁሌ ለምለም ነው
ለመልማለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ