አንተን ሳስብ
Anten Saseb
2014 · ትራክ 5 · 6:19 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተን ሳስብ ጌታ አንተን ሳስብህ
አንተን ሳስብ ገና አንተን ሳስብህ
ወደ አምልኮ ባሕር ጠልቄ እሰጥማለሁ
ወደ አንተ መገኛ አድራሻ እየገባሁ
ስራዬ ስራዬ ማምለክ ነው
በቅኔ አንተን መባረክ ነው
ይሄው ጀመረኝ ለማመስገን በቅዱስ ስምህ መጉአደዱ
ቁጥር 2 · Verse 2
እንዲህ ይበሉ ከእኔ ጋራ አንተን ለማምለክ የወደዱ (፪x)
ቅዱስ ቅዱስ ፊተኛ ኋለኛ
ያለህ የምትኖር እግዚአብሔር (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንኳን እውነተኛ የሁሉም ባለቤት ሲከተል ልብ ያውቀው
ሰው ያመልክ አይደል ወይ እስትንፋስ ከሌለው አምላክ አበጅቶ
እግዚአብሔር አምላክ ነው ለእኛም በራልን ሚለው ቃል ከገባኝ
ለክብርህ ልዘምር ከጣኦታት መንደር ክንድህ ስላወጣኝ
አንተን ሳመልክህ ደስታ ቢያደርገኝ እንደሰከረ
ይሄ ጥቂት ነው ከዚህ ይብሳል እየጨመረ
ጌታ ሳመልክ ደስታ ቢያደርገኝ እንደሰከረ
ይሄ ጥቂት ነው ከዚህ ይብሳል እየጨመረ
ቁጥር 4 · Verse 4
ይሄው (፬x) የአንተን ምሥጋና ጌታ ኢሄው
ይሄው (፬x) የአንተን አምልኮ ጌታ ኢሄው
የአንተን ምሥጋና ጌታ ኢሄው
የአንተን አምልኮ ጌታ ኢሄው
የአንተን ምሥጋና ጌታ ኢሄው
የአንተን ዝማሬ ጌታ ኢሄው
ቁጥር 5 · Verse 5
አንተን ሳስብ ከጭንቀት ጐጆ ስር ወጥቼ በማመስገን ክንፍ እበራለሁ
አንተን ሳስብ ከፍ ያለብኝን በሙሉ ወደታች ማየት እጀምራለሁ
አንተን ሳስብ ማጉረምረም ግቢ እኮ አይደለም ውሎ ማደሪያ ሰፈሬ
አንተን ሳስብ ጌጠኛ ልብሴን ለብሼ ቅዱስ ነው ሚልህ መዝሙሬ
አዝማች · Chorus
ቅዱስ ቅዱስ ፊተኛ ኋለኛ
ያለህ የምትኖር እግዚአብሔር (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ነፍሥም አይቀርልኝ የአንተን ማንነት ክብርህን አስቤ
ቅዱስ ሊል ይፈጥናል ታላቅነትህን ሊያመሰግን ልቤ
የምሥጋና ሽቶ ሳልቆጥብ ሳልሰስት ለክብርህ ላፍሰው
እንኳን ለደቂቃው ፳፬ ሰዓቱን ባመልክህ ሲያንስህ ነው
የሰራኸኝ የፈጠርከኝ ለዚህ ነውና
ፈጽሞ አልጠግብም ዘምሬ አውርቼ የአንተን ምሥጋና (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
አንተን ሳስብ ከጭንቀት ጐጆ ስር ወጥቼ በማመስገን ክንፍ እበራለሁ
አንተን ሳስብ ከፍ ያለብኝን በሙሉ ወደታች ማየት እጀምራለሁ
አንተን ሳስብ ማጉረምረም ግቢ እኮ አይደለም ውሎ ማደሪያ ሰፈሬ
አንተን ሳስብ ጌጠኛ ልብሴን ለብሼ ቅዱስ ነው ሚልህ መዝሙሬ
አዝማች · Chorus
ቅዱስ ቅዱስ ፊተኛ ኋለኛ
ያለህ የምትኖር እግዚአብሔር (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ