ያን ዓመት እያስታወስኩኝ
Yan Amet Eyastaweskugn
2014 · ትራክ 6 · 5:06 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያን ዓመት እያስታወስኩኝ
ያንን ወር እያስታወስኩኝ
ያንን ቀን እያስታወስኩኝ
ከአውሬው አፍ በአንተ እንደዳንኩኝ
አዝማች · Chorus
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስንት መስከረም ስንት ጥቅምት
ከእባብ ከጊንጡ የዳንኩበት
ስንት ህዳር ነበር ስንት ታህሳስ
ከሞት ያዳንከኝ ደርሰህ ኢየሱስ
ስንት ጥር አልፏል ስንት የካቲት
አለቀልኝ ብዬ ያልኩበት
ስንት መጋቢት ስንት ሚያዚያ
ሃዘን ሲሆነኝ መውጫና መግቢያ
ግንቦትስ ሰኔ ሐምሌ ነሃሴ
የጭንቅን ቀን አይቷል ይህ ነፍሴ
በዚህ ሁሉ ግን ደርሰህ ያዳንከኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
እንዳመሰግን ዛሬን ሰጠኸኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በጠዋት በቀትር ባመሻሽ በሌሊት
ስራህን ለማሰብ ብራመድ የኋሊት
ትዝ የሚሉኝ ማስታውሳቸው
የአንተን ማዳን ያየሁባቸው
እኮ እነዚያ የሄዱት አርቦች
ሃሙስ ቅዳሜ ብዙ እሁዶች
እሮቦቼ ማክሰኞ ሰኞ
ያልፍኳቸው ማዳንህ ገኖ
ይሁኑልኝ ለመታሰቢያ
የአንተን ማዳን ሁሌ ለማውሪያ
እንዲህ ልበል ክበር ተመስገን
በአንተ ምህረት አለፈ ያ ቀን
አዝማች · Chorus
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
በሌሊት ከእንቅልፌ በድንገት ስነቃ
ቀኑን ላለማየት እል ነበር ባልነጋ
ባልነጋ ስላልኩኝ መች ቀርቶ ሳይነጋ
ቀኑን እንዳዘንኩኝ እደርስ ነበር ምሸትጋ
በጉስቁልናዬ አዘንክልኝና
ለነፍሴ ሰጠሃት የመጽናናት መና
ሌሊቶቼም ሆኑ መዝሙር መቀበያ
ቀኖቼም የአንተን ፈቃድ ማገልገያ
አዝማች · Chorus
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ