Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይፈውስ ይዳሰኝ

Yefewes Yedasegn

2014 · ትራክ 1 · 5:08 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሳትነካኝ ሳትነካኝ አልውጣ ከዚህ

ሳትነካኝ አልውጣ ከዚህ

ይፈውስ ይዳሰኝ እጅህ (፬x)

እጅህ ነው የሚያጸናኝ የሚያጽናናኝ

እጅህ ነው ከስብራቴ ሚጠግነኝ

እጅህ ነው የሚያብስልኝ የልቤን እምባ

እጅህ ነው ደስታ ሚሰጠኝ ቤትህ ስገባ

ይፈውስ ይዳሰኝ እጅህ (፬x)

ላይ ላዬን ሳይሆን ልቤን የሚነካው

ጢሻውን ውስጠቴን በፍቅር ሚያንኳኳ

ሚነቀል ነቅሎ ሚተከል ተክሎ

የሚለውጠኝ ሌላ አድርጐ

እጅህ እጅህ የእኔ ወዳጅ እጅህ

እጅህ እጅህ የእኔ ወዳጅ እጅህ

ይፈውስ ይዳሰኝ እጅህ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ