አይቼዋለሁ
Ayechiewalehu
ትራክ 6 · 7:33 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔም እንዲህ እንዲህ ወግ ደረሰኝ
ከመቅበዝበዝ እርሱ በቃህ ሲለኝ
ያ መራራ ሕይወቴ ጣፈጠ
በኢየሱሴ ታሪክ ተለወጠ
አዝማች · Chorus
አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ
አይቼዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው
እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ
እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔስ ገና ገና በልጅነት
አይቻለሁ የጌታዬን ምህረት
ሲርበኝም ከእጁ በልቻለሁ
ያንን ሁሉ መች እዘነጋለሁ
አዝማች · Chorus
አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ
አይቼዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው
እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ
እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ማን ልበለው ምን ለበለው (፪x)
በምን ቋንቋ በምን አንደበት
ይነገራል የርሱ ደግነት (፪x)
አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ
እኔ አውቀዋለሁ እኔ አውቀዋለሁ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ