ልባርከው
Lebarkew
ትራክ 4 · 5:33 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እስኪ ስሙኝ አንዴ ስሙኝ ልንገራችሁ
ምስኪኑን ሲያከብር በዓይናችሁ ያያችሁ
ኧረ ምን ይባላል ምንስ ይነገራል
አምላክ ሥራው ብዙ ይህንን አድርጓል (፪x)
እስኪ እንደ ጌታ ማን አለ (፫x)
እንደ እርሱ ያለ ማን አለ (፫x)
ጌታ ልዩ ነው ልዩ ነው
እርሱስ ልዩ ነው ልዩ ነው
በእርግጥ ልዩ ነው ልዩ ነው
ልዩ ነው እኩያ የለው
እንደ አባትም ሆኖ ከአባትም በላይ
ብዙ አድርጐልኛል ኢየሱስ ኤልሻዳይ
እንዴት እችላለሁ በቃላት ዘርዝሬ
ሥሙን አከብራለሁ ይኸው በዝማሬ
አዝማች · Chorus
ልባርከው ጌታዬን ልባርከው
ልባርከው ኢየሱሴን ልባርከው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሳልሰጋ እኖራለሁ በርሱ ተማምኜ
እጅግ በሚመቸው ትከሻው ላይ ሆኜ
እኔ አልጨነቅም ምድር ቢነዋወጥ
የማመልከው አምላክ ፈፅሞ አይለዋወጥ
አዝማች · Chorus
ልባርከው ጌታዬን ልባርከው
ልባርከው ኢየሱሴን ልባርከው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወጀቡ ቢነሳ ከቶ አያሰጥመኝም
ከኢየሱሴ ፍቅር ምንም አይለየኝም
የተናገረኝን እንደሚፈፅመው
ሁልጊዜ አምነዋለሁ አምላኬ ታማኝ ነው
አዝማች · Chorus
ልባርከው ጌታዬን ልባርከው
ልባርከው ኢየሱሴን ልባርከው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የእግዚአብሔርን ክንድ ማን ይከለክላል
በብርታትስ በልጦት ማንስ ያቆመዋል
ሁሉን እየረታ ሲሰራ የኖረው
እንደ ትላንትናው ዛሬም ጌታ ያው ነው
አዝማች · Chorus
ልባርከው ጌታዬን ልባርከው
ልባርከው ኢየሱሴን ልባርከው (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እንዳንተ ያለ ማን አለ (፫x)
እንዳንተ የሚሆን ማን አለ (፫x)
ጌታ ልዩ ነህ ልዩ ነህ
ኢየሱስ ልዩ ነህ ልዩ ነህ
አንተስ ልዩ ነህ ልዩ ነህ
ልዩ ነህ እኩያ የለህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ