Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅርህ ማርኮኛል

Feqreh Markognal

ትራክ 7 · 6:15 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሥምህ በከንፈሬ ላይ ይጣፍጠኛል

ልቤ ገና ሲያስብህ ሃሴት ያደርጋል

እውነት ኢየሱስ ጌታ ወድጄሃለሁ

ፍቅርህ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ (፯x)

ስላንተ ማውራት አይሰለቸኝም

ስምህን ሳነሳ ብውል አልጠግብህም

ውበትህን ፍፁም አደንቀዋለሁ

መልካምነትህን እተርካለሁ (፭x)

ሥምህ በከንፈሬ ላይ ይጣፍጠኛል

ልቤ ገና ሲያስብህ ሃሴት ያደርጋል

እውነት ኢየሱስ ጌታ ወድጄሃለሁ

ፍቅርህ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ (፯x)

ተማርኬያለሁ ስቦኛል ፍቅርህ

ከእግርህ ስር ጥሎኛል እንዲገዛልህ

ያንተ ምርኮኛ ተረጂ ሆኛለሁ

እንደወደድክ አርገኝ ተማርኬያለሁ (፭x)

ሥምህ በከንፈሬ ላይ ይጣፍጠኛል

ልቤ ገና ሲያስብህ ሃሴት ያደርጋል

እውነት ኢየሱስ ጌታ ወድጄሃለሁ

ፍቅርህ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ (፯x)

በመስቀል ላይ ሆኖ ነፍሱን ለኔ ሰጥቶ

ታደገ ጌታዬ በእኔ ፈንታ ሞቶ

ከዚህ ሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለው

የጌታዬ ኢየሱስ ኧረ ልዩ ነው (፭x)

ሥምህ በከንፈሬ ላይ ይጣፍጠኛል

ልቤ ገና ሲያስብህ ሀሴት ያደርጋል

እውነት ኢየሱስ ጌታ ወድጄሃለሁ

ፍቅርህ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ (፯x)

ተማርኬያለሁ (፰x)

ኧረ ልዩ ነው (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ