ጌታ ተመሥገን
Gieta Temesgen
ትራክ 5 · 4:36 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክበርልኝ ብዬ ገና አልጠገብኩም
ንገሥልኝ ብዬ በልቤ አልረካሁም
ከምሥጋና ሌላ ምን አለ ምትወደው
ባቀርብልህ ጌታ ከምንም ባልሰለቸሁ (፪x)
ቅዱስ ቅዱስ ብለው ሁሌ ከሚያከብሩህ
እኔን ከመደብከኝ ከሚያመሰግኑህ
ጥማቴ ይሄ ነው እኔ አከብርሃለሁ
በቀንም በሌሊት ምሥጋና እሰዋለሁ
አዝማች · Chorus
ብቻ አንተ ከወደድከው
ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰማይና ምድር ክብርን ያወራሉ
እግዚአብሔር ትልቅ ነው ትልቅ ነው እያሉ
እኔም በተራዬ ለትውልድ ልናገር
የሚመስልህ የለም ወዳጄ ሆይ ክበር
አዝማች · Chorus
ብቻ አንተ ከወደድከው
ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፊትህን ወደ እኔ መልሰሃልና
የአንተ ወገን አርገህ ዋጅተኸኛልና
ከምርጦችህ ጋራ እኔም ተስማምቼ
እሰግድልሃለሁ መቅደስህ ገብቼ
አዝማች · Chorus
ብቻ አንተ ከወደድከው
ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የምለው ብዙ አለኝ ስላንተ ማወራው
አምላኬ ይሄ ነው ብዬ የምናገረው
የሚሰማኝና የሚያየኝ ያክብርህ
የእኔ ብቻ አይበቃም ዘሬም ይገዛልህ
ክበርልኝ ብዬ ገና አልጠገብኩም
ንገሥልኝ ብዬ በልቤ አልረካሁም
ከምሥጋና ሌላ ምን አለ ምትወደው
ባቀርብልህ ጌታ ከምንም ባልሰለቸሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ብቻ አንተ ከወደድከው
ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ