ገና አለኝ ምሥጋና
Gena Alegn Mesgana
ትራክ 2 · 5:15 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ ተመሥገን (፰x)
ዛሬም ተመስገን ነገም ተመሥገን
ሁሌም ተመሥገን (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ባህሩን በኃይል ከፈልከው (ተመሥገን)
ሕዝብህን በድል መራኸው (ተመሥገን)
ጠላት ጉልበቱ ተመትቶ (ተመሥገን)
አይተናል ከባሕር ሰጥሞ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ ተመሥገን (፰x)
ዛሬም ተመስገን ነገም ተመሥገን
ሁሌም ተመሥገን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሃያ አራት ሽማግሌዎች ወድቀው ክብር ይሰጡሃል
መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ይገባል ለአንተ ይሉሃል
እኔም ባለችኝ ጊዜ ላክብርህ ውዱ ጌታዬ
ምሥጋና ምሥጋና እላለሁ ጌታ ነህ ባለ ውለታዬ
ገና አለኝ ምሥጋና ገና (፬x)
ገና ገና መቼ ይበቃውና
ገና ገና ዛሬም እንደገና
ገና ገና እሰዋለሁ ገና (፪x)
አልጠግብ ባመሰግነው ተመሥገን ተመስገን ብለው
ኢየሱሴ ለኔ ያረገው ውለታው እጅግ ብዙ ነው
አልውልም ሳላነሳሳው ሥሙ እንደሚፈስ ዘይት ነው
እንደገና አከብረዋለሁ ምሥጋናዬ እስኪ ይድረሰው
ገና አለኝ ምሥጋና ገና (፬x)
ገና ገና መቼ ይበቃውና
ገና ገና ዛሬም እንደገና
ገና ገና እሰዋለሁ ገና (፪x)
ገና አለኝ ምሥጋና ገና (፬x)
ገና ገና መቼ ይበቃውና
ገና ገና ዛሬም እንደገና
ገና ገና እሰዋለሁ ገና (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ