ይገርማል
Yigermal
ትራክ 3 · 6:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እዚህ እደርሳለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም
ከቶ በእኔ ጉልበት የሚቻል አይደለም የሚሆን አይደለም
እርሱ በፈቃዱ ይህን ካደረገው
ከመገረም ውጪ ሰዎች ምን እላለሁ እኔ ምን እላለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ
ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል
ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ
ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል
ቁጥር 2 · Verse 2
አይደንቃችሁም ወይ ወገኖች በሙሉ
ጌታ ያደረገው ለእኔ ለምስኪኑ
እርሱ በኔ ሊከብር መስዋዕቴን ወዶታል
በደረቁ አጥንቴ ዝማሬን ጨምሯል
አዝማች · Chorus
ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ
ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል
ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ
ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል
ቁጥር 3 · Verse 3
ያዩኝ ይደነቁ እዚህ በመድረሴ
በእርሱ ሆኖልኛል አይደለም በራሴ
የማላገኘውን ዘመኔን ብሰራ
ጌታ አደረሰኝ እስከ ጺዮን ተራራ ይገርማል
አዝማች · Chorus
ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ
ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል
ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ
ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል
ቁጥር 4 · Verse 4
ከዘመን ዘመናት ወደዚህ አሻግሮ
ቀድሞ እሱ ያየውን በልጁ ሰውሮ
ዛሬ ተገለጠ ፍፃሜው አማረ
ስንቱን ጉድ አሰኘ ስንቱ ተገረመ ይገርማል
አዝማች · Chorus
ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ
ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል
ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ
ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል
ቁጥር 5 · Verse 5
የሚያየኝ ያክብርህ ይደነቅብህ
በእኔ በትንሹ ስትሰራ ያየህ
ይናገር ክብርህን ምሥጋና ይጨምር
ያው ነህ ለዘላለም ወዳጄ ሆይ ክበር ይገርማል
አዝማች · Chorus
ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ
ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል
ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ
ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል
ቁጥር 6 · Verse 6
አደንቅሃለሁ አደንቅሃለሁ
ያለኝ ይሄ ነው ከተቀበልከው አመልክሃለሁ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
ያለኝ ይሄ ነው ከተቀበልከው አመልክሃለሁ
እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ቋንቋዬ ይህ ነው ከተቀበልከው እወድሃለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ