እጠብቃለሁ
Etebeqalehu
ትራክ 11 · 5:56 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ ከአንተ የት እሄዳለሁ
እጠብቃለሁ ዛሬም እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ ከአንተ የት እሄዳለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በለስ እንኳን ባያፈራ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ
ወይን ፍሬ ባይጐመራ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ
ከብቶች በጋጡት ባይኖሩ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ
እርሾች ምግብን ባይሰጡ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ
አዝማች · Chorus
እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ ከአንተ የት እሄዳለሁ
እጠብቃለሁ ዛሬም እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ ከአንተ የት እሄዳለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ አንተ ግን አንተ ነህ
አንተ ጊዜ የማይልውጥህ
አንተ ዘግይተህ ተነስተህ
አንተ ቀድመህ ትደርሳለህ (፪x)
ያኔ በሸለቆ ደግሞም በተራራ (፪x)
ወየው ጠፋሁ ብዬ አምላኬን ስጣራ (፪x)
በጨነቀ ጊዜ ተገልጦ አይቻለሁ
ስጋት አይገባኝም ዛሬም አምነዋለሁ ፣ ዛሬም አምነዋለሁ (፪x)
ይረዳኛል አምናለሁ ይረዳኛል (፪x)
ያግዘኛል አምናለሁ ያግዘኛል (፪x)
ይረዳኛል አምናለሁ ይረዳኛል (፪x)
ያግዘኛል አምናለሁ ያግዘኛል (፪x)
አንገቴን አልደፋም አጋዥ እንደሌለው
እንደ ብርቱ ጌታ ኢየሱስ ከኔ ጋር ነው
ለምን መቆዘሜ ሃሳቢ እንደሌለው
የነአብርሃም አምላክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው (፪x)
ይረዳኛል አምናለሁ ይረዳኛል (፪x)
ያግዘኛል አምናለሁ ያግዘኛል (፪x)
አንተ አንተ ግን አንተ ነህ
አንተ ጊዜ የማይልወጥህ
አንተ ዘግይተህ ተነስተህ
አንተ ቀድመህ ትደርሳለህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ