ባነበብነው በሰማነው
Banebebnew Besemanew
2001 · ትራክ 9 · 5:25 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ
ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ
ቁጥር 1 · Verse 1
እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች አሉ በዙሪያችን
እኛም ደግሞ ሃያል ክንድህ ድንቅ አድርጐ አይተናል በዓይናችን
እግዚአብሔር ታላቅ ነህ ከምንልህ በላይ
ሥምህ ብሩክ ይሁን በምድር በሰማይ (፪x)
አዝማች · Chorus
ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ
ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ
ቁጥር 2 · Verse 2
በነፍሳችን እንዳንዝል እንዳንደክም ደግፎ የሚያቆመን
ለአንድ አፍታም የማንረሳው የማንጥለው ድንቅ ታሪክ አለን
የነገው ደመና የሚያጨልመው ነገር
አይከለክለንም አንተን ከማመስገን (፪x)
አዝማች · Chorus
ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ
ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ
ቁጥር 3 · Verse 3
አይተንሃል ፣ ሰምተንሃል ፣ ዳሰንሃል ፣ እንመሰክራለን
እንደ ጠላታችን ምኞት አልጠፋንም ዛሬም በሕይወት አለን
በሆነልን ነገር ብዙ ተደንቀናል
የአባታችን መንግሥት ገና ይጠብቀናል (፪x)
አዝማች · Chorus
ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ
ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ጻድቅ ፈራጅ እውነተኛ ፣ ፊትን አይተህ ፈጽሞ አታደላ
ፀሐይ ለጠለቀችበት ለጨነቀው ፣ ትሰጣለህ መላ
ጊዜ ደረሰና ሁሉም ልኩ ታውቋል
የሳቀ ሲያለቅስ ፣ ያለቀሰም ስቋል (፪x)
አዝማች · Chorus
ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ
ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ