ጌታ ተባረክ
Gieta Tebarek
2001 · ትራክ 6 · 3:55 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠራኸኝ ከዚህ ክፉ ዓለም
ነፍሴን አዳንካት ዘለዓለም
ከዚህ የበለጠ ደስታ ምንም የለም
ይኸው ሞላልኝ ስለቴ
ክበር ከፍ በል በህይወቴ
ለአንተ ክብር ይዋል መላው እኔነቴ
አዝማች · Chorus
ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
ቁጥር 2 · Verse 2
በክቡር ደምህ አንጽተህ በመንፈስ ቅዱስ ቀብተህ
አገልጋይ አረግኸኝ ጸጋን ከላይ ሞልተህ
ለስምህ ክብር ልዘምር በምሥጋና ላይ ልጨምር
ላቆምኸኝ ላምላኬ ይሁን ለአንተ ክብር
አዝማች · Chorus
ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጠላት ቢነሳ በአመጻ ቢወረውርም ፍላጻ
ቆምኩኝ እስከዛሬ ከአንተ የተነሳ
ክረምት ከበጋ አለፈ ቃልኪዳንህ መች ታጠፈ
አንተን በእኔ ላይ ሲያይ ሁሉም ተሸነፈ
አዝማች · Chorus
ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
ቁጥር 4 · Verse 4
የሶሪያ ንጉሥ ደማስቆ
ሴራ ተንኮሉን ማን አውቆ
አልሞ ነበር ሊይዘኝ አሾልቆ
አንተ ግን አታጣ መላ
ለባሪያህ ሆንኸኝ ከለላ
አተምከው ዙሪያዬን በእሳት ሰረገላ
አዝማች · Chorus
ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ