ጌታዬ በአንተ ነው
Gietayie Bante New
2001 · ትራክ 12 · 4:36 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና
እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና
እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል
ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከታላላቆች ከአለቆች ጋራ
ፊት ለፊት ቆሜ እኩል ላወራ
ስለሆንክልኝ ግርማ ሞገሴ
ከፍ በልልኝ ጌታ ኢየሱሴ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና
እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና
እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል
ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አድነኸኛል ከሰቆቃዬ
በአንተ መጽናናት ደርቋል እንባዬ
አቁመኸኛል በተራራ ላይ
አብቅተኸኛል ክብርህን እንዳይ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና
እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና
እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል
ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በአንተ ለምልሟል ምድረ በዳዬ
በረከት ሞልቷል የሕይይወት ጓዳዬ
ላይ ታች ከማለት ከሩጫ አርፌ
መብላት ጀመርኩኝ እሸት ቀጥፌ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና
እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና
እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል
ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ዛሬስ ጠላቴ ሥፍራውን ለቋል
ከላይ የነበር ከእግሬ ሥር ወድቋል
በአንተ ጀግንነት ነጻ ወጣሁኝ
አንተ ስትከብር እኔም ከበርኩኝ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና
እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና
እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል
ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ