ድካሜን አንሳ ከላዬ
Dekamien Ansa Kelayie
2001 · ትራክ 1 · 4:09 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ
ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ግብረ ጉንዳን መኖዋን በበጋ አሰናድታ
ክረምት በመጣ ጊዜ ትበላለች ተኝታ
ጻድቅ በምቹ ጊዜ በአንተ ፊት ከተጋ
ዋስትና አለውና ይኖራል ምንም ሳይሰጋ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ
ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ካልተጠበቀ መንጋ ማነው ወተት የሚሻ?
ያልዘሩትን ለማጨድ አይኬድም ወደ እርሻ
ጥያቄ በመጣ ጊዜ እምነቴ እንዳይከዳኝ
ዛሬ ቀን ሳለ ጌታ ፍቃድህን ልፈጽም እርዳኝ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ
ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ትጥቄን ሳላጠባብቅ እንዲያው መሮጥ ካሰኘኝ
ተጠልፌ ወድቄ ጠላት እንዳያገኘኝ
ዛሬ ስራኝ በጓዳ በአደባባይም አይደል
ኋላ አያቅተኝም በአንድ ጠጠር ሺህ መግደል
አዝማች · Chorus
አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ
ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከተከፈተ ሰማይ ወርቃማ ቅባት ፈሶ
ጸጋህ በውስጤ ይሙላ መንፈሴን አረስርሶ
ደዌን እገስጻለሁ መናፍስትን አዛለሁ
ጭፍሮችን አባርሬ ምርኮን እበዘብዛለሁ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ
ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ