አውርቼ አልጨረስኩም
Awrechie Alchereskum
2001 · ትራክ 8 · 3:30 · አማርኛ
ለአሉባልታ ጊዜ የለኝ እኔ
አውርቼ አልጨረስኩ ስለመዳኔ
አልጣላ ሁሉም የመጣው ከአንተ በኋላ
በመቦጫጨቅ ባርኮት አይመጣ
ለውኃ ጥማት ውኃ አይጠጣ
እስኪ እንጨብጥ እርፍ ማረሻ
ሥራ ነውና የአገር መነሻ አሀ አሀ
አርሰን ሳንዘራ መስከረም ጠባ
አገር በወሬ አትገነባ
ነገም እንዳያልፍ እንደ ትላንቱ
ጉልበት ማንቃቱ
ከአየር ከውሃው ምንም አላጣን
ስላልሰራን ነው ረሃብ የቀጣን
የሞተው ሞቶ ያለነው አለን
ታጥቀን ከወጣን ነገ እንደርሳለን አሀአሀ
መስመር ጠብቆ ሮጦ ማሸነፍ
ወይስ በተንኮል ወንድምን መጥለፍ
የትኛው ይሆን የተፈቀደው
እኔ ትቻለሁ ህሊና ይፍረድ
እጣ የደረሰው ትላንት ተገፋ
ዛሬስ ማን ይሆን ባለወረፋ
እግዚአብሔር ሆይ እየን ከሰማይ
የፍቅር ዘይት አፍስስ በእኛ ላይ
የወሬ ጠላት ሥራን አፍቃሪ
በውኃ በየብስ በአየር በራሪ
የትውልድ ኩራት መድሃኒተኛ
አምላካችን ሆይ አምጣልን ለእኛ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ