በዚህ ዘመን
Bezih Zemen
2001 · ትራክ 10 · 4:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (፪x)
ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል
ቁጥር 1 · Verse 1
ኃጥያት በትር ይዞ ኦሆሆ አደባባይ ወጣ አሃሃ
የሚቃወሙትን እኽኽ በችጋር ሊቀጣ አሃሃ
ክፉዎች ሲደላቸው ኦሆሆ ጻድቃን ሲቸገሩ አሃሃ
ተገለባበጠ እኽኽ እንዴት ነው ነገሩ
አዝማች · Chorus
በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (፪x)
ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል
ቁጥር 2 · Verse 2
ሃሰት ሲደራርብ እኽኽ በሹመት ላይ ሹመት አሃሃ
እውነት ተናጋሪ እኽኽ ጠላት ሲበዛበት እኽኽ
ደሆች ሲነቀሉ ኦሆሆ ከቤት ከርስታቸው እኽኽ
ጻድቅ ፈራጅ አምላክ አሃሃ ተሟገትላቸው አሃሃ
አዝማች · Chorus
በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (፪x)
ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል
ቁጥር 3 · Verse 3
አውሬው ሲያቆጠቁጥ እኽኽ ሥሩን ሲዘረጋ አሃሃ
ሃሰተኛው መሲሕ እኽኽ አጃቢ ሲያንጋጋ አሃሃ
ጊዜውን ካልመረመርን ዘመኑን ካልዋጀን አሃሃ
የተወሰድን እንደሆን ኦሆሆ ሰዎች ምን ሊበጀን አሃሃ
አዝማች · Chorus
በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (፪x)
ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል
ቁጥር 4 · Verse 4
መዝናናት አበዛን እኽኽ መዋጋት ትተናል አሃሃ
ያለነው ጦር ሜዳ አሃሃ መሆኑን ረስተናል እኽኽ
እስኪ እንበርከክ እኽኽ ወደ እልፍኝ እንግባ እኽኽ
ሰይጣን ጸሎት እንጂ አሃሃ አይፈራም ጭብጨባ አሃሃ
አዝማች · Chorus
በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (፪x)
ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ