Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ላደረክልኝ የምመልሰው

Ladereklign Yemimelisew

2001 · ትራክ 11 · 5:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ላደረግህልኝ የምመልሰው

አንዳች የለኝም እጄም ባዶ ነው

እንካ ተቀበል የአፌን ምሥጋና

በእጄ ያለው ይኸው ነውና (፪x)

አንደበት የለኝ ሥምህን ልጠራ

ምላስም የለኝ ሥራህን ላወራ

ልናገርም ብል ጊዜም አይበቃ

ተመስገን ብዬ በአጭሩ ላብቃ (፪x)

ላደረግህልኝ የምመልሰው

አንዳች የለኝም እጄም ባዶ ነው

እንካ ተቀበል የአፌን ምሥጋና

በእጄ ያለው ይኸው ነውና (፪x)

በፍቅር ቃልህ ልቤን ስትመታ

ነፍሴን ሥጋዬን ከእስር ስትፈታ

ምን አለኝና ምኔን ልክፈልህ

ከተቀበልኸኝ ክበር ልበልህ (፪x)

ላደረግህልኝ የምመልሰው

አንዳች የለኝም እጄም ባዶ ነው

እንካ ተቀበል የአፌን ምሥጋና

በእጄ ያለው ይኸው ነውና(፪x)

ከትቢያ አንስተህ ሰው ስታደርገኝ

በነፍስ በሥጋ ስትባርከኝ

ሰማያዊ ፍቅርህ ልቤን ሲሞላ

ተመስገን እንጂ የለኝም ሌላ(፪x)

ላደረግህልኝ የምመልሰው

አንዳች የለኝም እጄም ባዶ ነው

እንካ ተቀበል የአፌን ምሥጋና

በእጄ ያለው ይኸው ነውና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ