ጌታዬን ያገኘሁ ቀን
Gietayien Yagegnehu Qen
2001 · ትራክ 3 · 5:54 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ
ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን
ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን
ቁጥር 1 · Verse 1
ሃይማኖት አለኝ ስል ስገበዝ ከርሜ (፪x)
መጠውለጉን ሳላውቅ ቅጠል አገልድሜ (፪x)
እርቃኔ ሲገለጥ እፍረት ያዘኝና (፪x)
ወደ ጌታ ሮጥኩኝ መሃሪ ነውና
አዝማች · Chorus
የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ
ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን
ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰው በእህል አይጠግብም ውሃም አያረካው (፪x)
የእግዚአብሔር ቃል በፍቅር ካልነካው (፪x)
ጤና ነኝ እያለ እራሱን ያስታል (፪x)
ቀን ቀን በሳቀበት ማታ ያቃስታል
አዝማች · Chorus
የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ
ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን
ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን
ቁጥር 3 · Verse 3
ታሪክ ያለኝ ይመስል በከንቱ ስኮፈስ (፪x)
ቀራንዮን ትቼ ታቹን ስመላለስ (፪x)
ጫማዬን ስጨርስ በሸለቆ ድንጋይ (፪x)
የመለኮት ጥሪ መጣልኝ ከሰማይ
አዝማች · Chorus
የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ
ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን
ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን
ቁጥር 4 · Verse 4
አልጋዬ ቆርቋሪ እንቅልፍ የማይሰጠኝ (፪x)
ምንድነው እንደዚህ የሚያገላብጠኝ (፪x)
እያልኩኝ ስመረር ኢየሱስ ደረሰ (፪x)
የሰላም አሸንዳ በላዬ አፈሰሰ
አዝማች · Chorus
የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ
ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን
ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን
ቁጥር 5 · Verse 5
ቀኒቷም ትባረክ ጌታን ያየሁባት (፪x)
ከዘመናት እስር የተፈታሁባት (፪x)
የምስራች ያለኝም እርሱን ጌታ ይክፈለው (፪x)
ጌታ እኔን ሲሸልም ለእርሱም አክሊል አለው (፪x)
አዝማች · Chorus
የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ
ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን
ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ