በአንተ ነው
Bante New
2005 · ትራክ 7 · 5:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማልጄ ደግሞ ስነሳ ስለውለታህ ላነሳሳ
ሌቱም አልበቃ አልበቃ አለኝ
ቀኑም እጥር እጥር አለብኝ
የተደረገልኝ ራሴው ነው የማውቀው
ዛሬ እዚህ መድረሴ ጌታዬ በአንተ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሳስበው የትላንቱን (አሃሃ)
አሰቃቂ መንገዱን (ኦሆሆ)
በፀጋህ ደገፍከኝና (አሃሃ)
ገረመኝ አለፍኩትና (፪x)
በአንተ ነው የእኔ ጌታ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እረካሁ ከእጅህ ጠጥቼ (አሃሃ)
ወጣሁት ጉልበት አግኝቼ (አሃሃ)
አልቀረሁ በምድረ በዳ (አሃሃ)
አትወድም ሰው እንዲጐዳ (አሃሃ) (፪x)
አዝማች · Chorus
በአንተ ነው የእኔ ጌታ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ ለእኔ ለእኔ የምታስበው መልካም ነዉ
ጌታ ለእኔ የምታስበው መልካም ነዉ
ቆጥሬው ተናግሬው (አሃሃ)
ከውስጤ የማይወጣው (አሃሃ)
ጌትዬ ለእኔ ያደረገው (አሃሃ)
ከቁጥር ያለፈ ነው (አሃሃ) (፪x)
አዝማች · Chorus
በአንተ ነው የእኔ ጌታ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ