ተናግሬ ነበር
Tenagerie Neber
2005 · ትራክ 10 · 5:35 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተናግሬ ነበር አስቀድሜ እኔማ
ድሉ የኔ ነው ስል ጠላቴም አልሰማ
እኔ አልመለስም ደጁ ጋር ደርሼ
ድርሻዬን እወስዳለሁ ምድሪቷን ወርሼ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምነው ተከተለኝ ጠላቴ ከኋላ (፫x)
ተው አትከተለው ሃይ የሚለው ጠፋ (፫x)
ቃል ይዤ መውጣቴን ዘንግቶት ነበረ (፫x)
እኔ ተሻገርኩኝ እርሱ ሰምጦ ቀረ (፫x)
ፋንታዬ ነው ከፍ ማለት ለኔ
አሃ ለኔ አሃሃ ለኔ (፪x)
ደመናዉ ከላዬ ላይ
ገለል ገለል ገለል አረክና (፪x)
አሻገርከኝ ይሄው ዛሬ
ይሄው ዛሬ በድሉ ጐዳና (፪x)
አዝማች · Chorus
ተናግሬ ነበር አስቀድሜ እኔማ
ድሉ የኔ ነው ስል ጠላቴም አልሰማ
እኔ አልመለስም ደጁ ጋር ደርሼ
ድርሻዬን እወስዳለሁ ምድሪቷን ወርሼ
ቁጥር 2 · Verse 2
ወደ ማዶ እንሂድ እንሻገር ሲለኝ (፫x)
ታንኳዬን ሊገፋት ንፋስ ተነሳብኝ (፫x)
ታዲያ ምን ጨነቀኝ ወጀቡ ቢበዛ (፫x)
ደንግጦ ይቆማል ጌታዬ ሲነሳ (፫x)
ፋንታዬ ነው ከፍ ማለት ለኔ
አሃ ለኔ አሃሃ ለኔ (፪x)
ደመናዉ ከላዬ ላይ
ገለል ገለል ገለል አረክና (፪x)
አሻገርከኝ ይሄው ዛሬ
ይሄው ዛሬ በድሉ ጐዳና (፪x)
ምነው ተከተለኝ ጠላቴ ከኋላ (፫x)
ተው አትከተለው ሃይ የሚለው ጠፋ (፫x)
ቃል ይዤ መውጣቴን ዘንግቶት ነበረ (፫x)
እኔ ተሻገርኩኝ እርሱ ሰምጦ ቀረ (፫x)
ፋንታዬ ነው ከፍ ማለት ለኔ
አሃ ለኔ አሃሃ ለኔ (፪x)
ደመናዉ ከላዬ ላይ
ገለል ገለል ገለል አረክና (፪x)
አሻገርከኝ ይሄው ዛሬ
ይሄው ዛሬ በድሉ ጐዳና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ