Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አለኝ የምለው

Alegn Yemelew

2005 · ትራክ 6 · 6:50 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የልብ ልቤን ላውጣው እስቲ ልናገር

ጌታ ያደረገልኝ አለኝ ብዙ የሚነገር

እርሱ ያደረገልኝ አለኝ ስሙኝ የሚነገር (፪x)

የእኔ ወዳጅ ነህ የእኔ የራሴ

መተኪያ የሌለህ ኢየሱሴ

ከስንቱ ቦታ ስንቱን አሻግረህ

ሊዚህ ያደረስከኝ አንተ እኮ ነህ (፪x)

ፀሐዩ ሲጠልቅ ጨለማው ሲመጣ

ንጉሥ ንጉሥን ሽሮ አንዱ በአንዱ ፈንታ

ለሁሉም ጊዜ አለው ጉልበቱ ሊፈታ

የማትለዋወጥ የማትቀያየር አንተ ብቻ ጌታ(፪x)

አለኸኝ የምለው

የእኔው ነህ የምለዉ

አንተኑ አንተኑ ነዉ

አንተኑ አንተኑ ነዉ (፪x)

የልብ ልቤን ላውጣው እስቲ ልናገር

ጌታ ያደረገልኝ አለኝ ብዙ የሚነገር

እርሱ ያደረገልኝ አለኝ ስሙኝ የሚነገር (፪x)

የእኔ ወዳጅ ነህ የእኔ የራሴ

መተኪያ የሌለህ ኢየሱሴ

ከስንቱ ቦታ ስንቱን አሻግረህ

ሊዚህ ያደረስከኝ አንተ እኮ ነህ (፪x)

ወንዝ አያሻግርም የቅርብ ወዳጅ ሆኖ

ፍቅር ዛሬ የለም ይላል ቀረ ድሮ

ሁኔታ ሲለወጥ ከአለበት ቦታ

የማትለዋወጥ የማትቀያየር አንተ ብቻ ጌታ(፪)

አለኸኝ የምለው

የእኔው ነህ የምለዉ

አንተኑ አንተኑ ነዉ

አንተኑ አንተኑ ነዉ (፪x)

አንተኑ አንተኑ ነዉ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ