መንፈስ ቅዱስ
Menfes Qedus
2005 · ትራክ 12 · 5:23 · አማርኛ
ግራ አይገባኝም አንተ እያለህ ጐኔ
ሁሌ ደስ ይለኛል መድህኔ ነህ ለእኔ (፪x)
አልጠፋ ብሎኝ ከአእምሮዬ (፪x)
ሁሌ ያዘምረኛል ውለታህ ጌታዬ (፪x)
ቢመዘን ከእንቁ ይበልጣል ለእኔ ያደረከው
ዛሬ እዚህ መድረሴ ዘመን መጥቶልኝ ነው
ምህረት በዝቶልኝ ነው
መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነህ
የእኔ ነህ (የእኔ ነህ) የእኔ መሪ ነህ
የእኔስ ጌታ ነህ (፪x)
የሩቅ አይደለህም የቅርቤ ነህ ለእኔ (፪x)
የሩቅ አይደለህም የግሌ ነህ ለእኔ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ