በሕይወት አለሁ
Behiwot Alehu
2005 · ትራክ 5 · 4:28 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ተወራረድኩበት በዚህ ታማኝ ጌታ
አይጥለኝም አልኩኝ እኔንም ለአንድ አፍታ (ኦሆ ለአንድ አፍታ)
የድሮ ቃልኪዳን በልቤ ውስጥ ገብቶ
ፎከርኩኝ በአምላኬ አይተወኝም ከቶ (ኦሆ እኔን ከቶ)
እንደ ዓይኑ እኔን ሲያይ
ገረመኝ ጌታ ከላይ
ምህረቱ ገንኖ ነው ለካ
አዝማች · Chorus
ያለፍኩት ያንን ጨለማ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዞር ዞር አልኩና ወደ ግራ ወደ ቀኝ (ወደ ግራ ወደ ቀኝ)
ከፊትም ከኋላም ሲጠፋ የሚረዳኝ (ሲጠፋ የሚረዳኝ)
ዓይኖቼን ሳነሳ ወደ የዋሁ ጌታ (ወደ ጀግናው ጌታ)
ችግሬን አጣሁት እሱን ባየሁ ለታ (እሱን ባየሁ ለታ)
ጌታ እንደሌለው እንደሌለው
እንደማንም እኔስ አይደለሁም
ቀና ስል ወደ ላይ ወደ አምላኬ
አዝማች · Chorus
ልመናዬን ሰማኝ ተንበርክኬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በቅጡ አውቀዋለሁ የኔን ጌታ
ያሻግራል ቃሉማ መልካም ቦታ
ሰንቆም ላከልኝ መልሴን ፈጥኖ
ያንን ክፉ ዘመን በቃ ብሎ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ምንድነው ሚሰማው በከተማው ወሬ
ሞቷል አትበሉ በሕይወት አለሁ ዛሬ (ኦሆ አለሁ ዛሬ)
እንደ እግዚአብሄር ሃሳብ ወደ ግብጽ ቢወርድም
ህልሙ ሳይፈጸም ባለራዕይ አይሞትም (በፍጹም አይሞትም)
አዝማች · Chorus
እንደ ዓይኑ እኔን ሲያይ
ገረመኝ ጌታ ከላይ
ምህረቱ ገንኖ ነው ለካ
ያለፍኩት ያንን ጨለማ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ