Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በአምልኮ

Beamleko

2015 · ትራክ 2 · 5:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በአምልኮ በዝማሬ በአምልኮ በዝማሬ አዬ

በአምልኮ በዝማሬ በአምልኮ በዝማሬ አዬ

ልምጣ ወደ አንተ አዎ ላሞካሽህ

ባማረው ዜማ ላቆላምጥህ (፪x)

ያማረውን መዝሙር ያማረውን ቅኔ

ገና እዘምራለሁ አልጠገብኩም እኔ (፪x)

ልቤ ነገረኝ (፬x) ልቤ ነገረኝ (፬x)

አንተ ወዳለህበት ወደአደባባይ ጌታ

የዳዊት አምልኮ የዝማሬው ሽታ

ልቤ ነገረኝ (፬x) ልቤ ነገረኝ (፬x)

ብቻ ኢየሱስ ቤቴ ካለ

ሙሉ ነው ይበቃኛል (፫x)

ብቻ ኢየሱስ ቤቴ ካለ

ሙሉ ነው ይበቃኛል (፫x)

ምሥጋና ለታረደው በግ ለታረደው

አምልኮ ለኢየሱስ ነው የሚገባው (፪x)

በአምልኮ በዝማሬ በአምልኮ በዝማሬ አዬ

በአምልኮ በዝማሬ በአምልኮ በዝማሬ አዬ

ልምጣ ወደ አንተ አዎ ላሞካሽህ

ባማረው ዜማ ላቆላምጥህ (፪x)

ብቻ ኢየሱስ ቤቴ ካለ

ሙሉ ነው ይበቃኛል (፫x)

ብቻ ኢየሱስ ቤቴ ካለ

ሙሉ ነው ይበቃኛል (፫x)

መዝሙር አለኝ ዜማ አለኝ

መዝሙር አለኝ የእኔ ጌታ ዜማ አለኝ

መዝሙር አለኝ ዜማ አለኝ

መዝሙር አለኝ የእኔ ጌታ ዜማ አለኝ

ያማረውን መዝሙር ያማረውን ቅኔ

ገና እዘምራለሁ አልጠገብኩም እኔ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ