Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መልካም ነህ

Melkam Neh

2015 · ትራክ 7 · 7:21 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አዝ፥ ኧረ አንተ መልካም ነህ መልካም

ለእኔ መልካም ነህ መልካም(፪)

ኧረ አንተ ልዩ ነህ ልዩ

ለእኔ ልዩ ነህ ልዩ(፪)

ብዙ ጊዜ ዘመርኩኝ ማንነትህ ገርሞኝ

ማቆም ይኸው አልቻልኩም ማምለኬን ቀጠልኩኝ

በምድር ላይ ቢፃፍ ባህር ቀለም ሆኖ

ያንተን መልካምነት አይገልፀውም ችሎ(፪)

እስከዛሬ ድረስ እኔ እስከማውቀው

የማይለወጥ ፊት ኢየሱስ ያንተ ነው(፪)

ያው ነህ ያው(4)

አዝ፥ ኧረ አንተ መልካም ነህ መልካም

ለእኔ መልካም ነህ መልካም(፪)

ኧረ አንተ ልዩ ነህ ልዩ

ለእኔ ልዩ ነህ ልዩ(፪)

ብዙ ጊዜ ዘመርኩኝ ማንነትህ ገርሞኝ

ማቆም ይኸው አልቻልኩም ማምለኬን ቀጠልኩኝ

በምድር ላይ ቢፃፍ ባህር ቀለም ሆኖ

ያንተን መልካምነት አይገልፀውም ችሎ(፪)

ለእኔ ምን አለኝ ምን አለኝ

ካንተ ሌላ ምን አለኝ[4]

እስከ ዛሬ ድረስ እኔ እስከማውቀው

የማይለወጥ ፊት እየሱስ ያንተ ነው

ያው ነህ ያው(4)

ስጋ ለባሽ ሁሉ ከብሩ እንደአበባ እንደሳር ሲረግፍ

ኧረ እንዴት መታደል ነው

ኧረ እንዴት ማረፍ ነው

በማታልፈው ጌታ ባንተ መደገፍ ነው[2]

ያው ነህ ያው(4)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ